የማህበረሰቡን አንገብጋቢ ጥያቄዎች፣ አስተያየቶችና ጥቆማዎች ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚችል እንዲሁም የእያንዳንዱን ጽ/ቤቶች ወቅታዊ መረጃዎች ለህዝብ ተደራሽ ማድረግ የሚችል ሲስተም በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት በማበልፀግ በክ/ከተማዉ ኢኖቬሽን ልማት ጽ/ቤት ተገመገመ። ይህ CEMS (Costemer Engagement Management System) የተሰኘ ሲስተም ከወረዳ እስከ ክ/ከተማ በየደረጃዉ ለነዋሪዎች ወቅታዊ መረጃዎች ከሚፈልጉት ተቋም በቀጥታ እንዲደርሳቸዉ የሚያግዝ፣ አስተያየት እና ጥቆማ በተለይም (በመልካም አስተዳደር፣ አገልግሎት አሰጣጥ፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራሮች )ላይ ሚስጥራዊነቱ በተጠበቀ መንገድ መስጠት እንዲችሉና ለጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ለመከታተል የሚያስችል መሆኑን የክ/ከተማዉ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ንጋቱ ጠቁመዉ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱን በማሳለጥ ዉስጥ ከፍተኛ አበርክቶ ያለዉና ህዝብን ከመንግስት የሚያቀራርብ በመሆኑን በሚመለከተዉ አካል እዉቅና ሲሰጠዉ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ገልፀዋል። የክ/ከተማዉ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበራ አባቢያ በበኩላቸዉ ቴክኖሎጂዎች በከተማ ደረጃ እዉቅና ተሰጥቷቸዉ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባቸዉ ጠቅሰዉ፤ የህብረተሰቡን ችግር የሚፈቱ፣ የመረጃ ተደራሽነትን የሚያሳልጡ፣ በመሆናቸዉ አዋጭነታቸዉ ተረጋግጦ ለአገልግሎት እንዲበቁ ጽ/ቤቱ ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል። ሰኔ 23/2017 ዓ.ም (አቃቂ ቃሊቲ)